Love8.me የአማርኛ እውቀት ማዕከል
ብቅ ባይ መስኮቶችና ያልተፈለጉ ትሮች
ብቅ ባይ መስኮት ገጽ ሲከፈት ወይም ሲጫኑ በተጨማሪ መስኮት የሚታይ ይዘት ነው። ከስርዓት ማሳወቂያ የተለየ ነው።
አይጫኑት
“ቫይረስ ተገኝቷል” ወይም “ሽልማት አሸንፈዋል” የሚል ብቅ ባይ መስኮት የሚጠይቀውን ፋይል አያውርዱ፣ መረጃም አያስገቡ።
ምንጩን ይለዩ
አንድ ጣቢያ ላይ ብቻ ከታየ ገጹን ይዝጉ። በብዙ ጣቢያዎች ላይ ከታየ የአሳሽ ቅጥያዎችንና የተጫኑ መተግበሪያዎችን ይመርምሩ።
ማገድና ማሳወቂያ
ብቅ ባይን በአሳሹ ማገድ ይቻላል። ከገጹ ውጭ የሚመጡ ማሳወቂያዎች ግን በማሳወቂያ ፈቃድ ውስጥ መዘጋት አለባቸው።
ተዛማጅ ንባብ
ምንጮችና ተጨማሪ ንባብ
አንዳንድ ምንጮች በእንግሊዝኛ ሊሆኑ ይችላሉ።